Here is my book, in Amharic, about the origin and development of main stream and radical Islam in Ethiopia. The book was in sell now both in Addis and here in diaspora. I believe it will be an eye opening one for Christians and modertae Muslims alike.
ይህ መጽሐፍ የአክራሪ እስልምናን ጥንተ መሠረትና አሁን ያለበትን ዕድገት በጥልቀት የዳሰሰ ነው፡፡ መጽሐፉን አንብቦ የጨረሰ ክርስቲያንም ሆነ በጎ ኅሊና ያለው ሙስሊም ሁሉ የወደፊት ሕልውናው አደጋ ላይ መሆኑን ስለሚገነዘብ የአክራሪ እስልምና ጉዳይ የእርሱም አጀንዳ እንደሆነ እንዲያስብ ይገደዳል፡፡ በተለይም ክርስትናን በመጀመሪያው ምእት በተቀበለችው በሀገራችን በኢትዮጵያ ላይ አክራሪዎች እያደረሱ ያሉትንና ወደፊትም የሚያደርሱትን በደል የሚያጋልጥ በመሆኑ እያንዳንዱ ክርስቲያንም ሆነ በጎ ኅሊና ያለው ሙስሊም ሁሉ ሊያነበው የሚገባ መጽሐፍ ነው፡፡
መምህር ብርሃኑ ጎበና
ሰባኬ ወንጌል፣ የነገረ ሃይማኖት መጻሕፍት ጸሐፊ
አክራሪነት በማናቸውም መሥፈሪያ ቢሆን የሚመሰገን ተግባር አይደለም፡፡ የእኔን እምነት እስካልተቀበልክ ድረስ እገድልሃለሁ፣ አጠፋሃለሁ የሚለው አመለካከት ከጤነኛ አእምሮ መውጣቱ ያጠራጥራል፡፡ የዚህ መጽሐፍ ደራሲ መረጃን ተንተርሰው፣ ታሪክን አጣቅሰው ተጠየቃዊ በሆነ መንገድ ያቀረቡልን ይህ መጽሐፍ ክርስቲያኑንም ሙስሊሙንም የሚጠቅም፣ ሁላችንንም ከፊታችን ስለተደቀነው አደጋ በርጋታ እና በቅንነት እንድንነጋገር የሚያደርግ ነው፡፡ ግልብነትን በመተው፣ መረጃን እና ቅን ኅሊናን በመንተራስ እንዲህ የሚጽፍ እና የሚናገር ቢኖር ችግሩን መፍታት በተቻለ ነበር፡፡ እባካችሁ ሌሎቻችሁም ችግሮቻችን ላይ በመጻፍና ለንባብ በማብቃት ድርሻችንን እንወጣ፡፡ የዚህ ጸጋው የሌለን ደግሞ በቅን ልብ በማንበብ እና ሌሎች እንዲያነቡ በማድረግ ድርሻችንን እንወጣ። ‹‹ያነበበ፣ የተረጎመ›› የሚለው እንዲደርሰን፡፡
ዳንኤል ክብረት (ዲያቆን)
የሥነ ቤተ ክርስቲያን ጥናት ተመራማሪ እና ጸሐፊ

ለምን ይህንን መጽሐፍ መጻፍ አስፈለገ? ርዕሰ ጉዳዩ እጅግ ጥንቃቄ የሚፈልግ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ በእሳት እንደ መጫወት ከእጅ ከወጣ ማጣፊያው የሚያጥር ዓይነት መሆኑም ይታወቃል፡፡ ነገር ግን ችግሩን እያዩ እንዳላዩ፣ እየሰሙ እንዳልሰሙ‹ እየሞቱ እንዳልሞቱ አድርጎ መቀበል ጅል ያሰኝ ካልሆነ በስተቀር ጠቢብም፣ አርቆ አስተዋይም፣ ለሀገር አሳቢም አያደርግም፡፡ አክራሪ እስልምና በኢትዮጵያ ውስጥ ከማቆጥቆጥም፣ ከመነሣሣትም አልፎ ተስፋፍቷል፡፡ ሥር እየሰደደ ለመሔዱ ስውር ማስረጃ ፍለጋ ከማይደከምበት ደረጃ ተደርሷል፡፡ ይህ መሆኑ ደግሞ ‹ሀገር ያወቀው ፀሐይ የሞቀው›፣ በቤተ መንግሥቱም በቤተ ክህነቱም የሚታወቅ የአደባባይ ምሥጢር ሆኗል፡፡ ሀገር ስላወቀው ፀሐይ ስለሞቀው ስለዚህ ችግር መጻፍ ‹እምነትን በእምነት ላይ ማነሣሣት› ነው የሚያሰኝ፣ ከጂሐዳዊ አክራሪነት ውጪ ያሉ ሙስሊሞችንም የሚያስከፋ አይሆንም፡፡ የሚፈለገው ነገር የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የተደገሰላትን እንድታውቅ፣ ጂሐዳዊነትን የሚቃወሙ ሙስሊሞች በስማቸው የሚፈጸመውን እንዲረዱ፣ መንግሥት በመንግሥትነቱ ፈር የለቀቀውን የአክራሪነት መስፋፋት ሃይ እንዲል መጠቆም ነው፡፡
ከመጽሐፉ የተወሰደ
Comments